Polly po-cket
free book gift

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።


Iqra

=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=

ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ


1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።

2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።

3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።

4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
Iqra
Iqra

Homeየወጣቱ ተልዕኮ ምንነትየአቂዳ ትምህርቶችየሶላት መመሪያረመዷንሙስሊም ሴቶችኢስላማዊ ቤተሰብከታሪክ ማህደርሐዲስለወጣቶችትምህርትና መሰረታዊ ክህሎታችጤናችንግጥምጥያቄና መልስኢስላማዊ መዝገበ ቃላት
free book gift

=<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=

ያ ሁሉን በፈጠረው ጌታህ ስም አንብብ!

free book gift

በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው።

free book gift

:☀:♥ የአብዱሏህ ቤተሰብ ታሪክ
የስኬት ጐዳና ♥:☀:


1976914 215022382024627 134976148 n

የአብዱሏህ ቤተሰብ ጠንካራ ሙስሊሞች ሲሆኑ በዚህ ታሪክ ሐዲ የተባለ የዘጠኝ ዓመት ልጅ አላቸው። ሐዲ በትመህርት ቤት የሚሰጡ ፈተናዎችንና አሳይመንቶችን ይፈራና ይጠላ ነበር። ስፖርት መጫወት በክፍል ውስጥ ካለው ውድድርና ተሳትፎ ስኬት የበለጠ ቀላልና ምቹ እንደሆነ ያስባል። ቤተሰቦቹ በዚህ ጉዳይ ላይ ይረዱት ዘንድ እንዲህ ሲል ይጠይቃል:-

ሐዲ: ሁልጊዜ ስኬታማ እንዴት መሆን እችላለሁ አባየ?

አባት: ከሁሉም በላይ ስለስኬት ልነግርህ የምችለው ፍቹን ከቁርአን በማየት ነው።

እናት: ባለፈው ዓመት ያጠናኸውን ሱራ ሸምስ ታስታው ሳለህ አይደለ? ስትል እናት ጠየቀችው

ሐዲ: እማየ እኔኮ የጠየኩት በትምህርቴ እንዴት ስኬታማና ተወዳዳሪ መሆን እንደምችል ነው።

አባት: እናውቃለን ትክክለኛ ስኬት ሊሳካ የሚችለው እራስን በመቆጣጠራና እራስን ወደ ትክክለኛ ጐዳና በመምራት እንደሆነ ስለምናምን ነው። ይህን የምታደርግ ከሆነ በትምህርት ቤት ብቻ አይደለም በሂወትህ ስኬታማ ትሆናለህ።

ሐዲ: እራስን መቆጣጠርና ወደ ትክክለኛ ጐዳና በመምራት ስትል ምን ማለትህ ነው አባየ?

አባት: ሂወታችን በፈተና የተሞላች ስትሆን ልክ እንደ ትልቅ ትምህርት ቤት ናት። ቁርአን እንደሚነግረን ለራሳችን ተዝኪያ የምናደርግ ከሆነ ፈተናውን እናልፋለን፤ ጀነትንም እንመነዳለን። ይህን ማድረግ ካልቻልን ወደ ጀሃነም እንወረወራለን።

እናት: በትክክል! ሐዲ ጀነት መግባት ትፈልጋለህ?

ሐዲ: አዎ እማየ! ነገርግን በትምህርት ቤቴም ስኬታማና ተወደዳዳሪ ከሆኑ ተማሪዎች መካከል መሆንም እፈልጋለሁ።

አባት: ተዝኪያ ካደረክ የተሻለ ነገር በትምህርት ቤት ማድረግ እንደምትችል ተስፋ አደርጋለሁ።

ሐዲ: ተዝኪያ ምንድ ነው አባየ?

አባት: በአረብኛ ተዝኪያ ማለት ሁለት ነገር ነው (1) ተዝኪያ ማለት እራስን ከመጥፎ ሃሳብና ስራዎች ማፅዳት ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ (2) ጥሩ እምነትንና ጥሩ ባህሪን ማበልፀግ ማለት ነው።

ሐዲ: አሁን ተረድቻለሁ ለራሴ ተዝኪያ ካደረኩ እራሴን ማሳደግና በትምህርቴም የተሻልኩ መሆን እችላለሁ ማለት ነው።

እናት: በትምህርት ቤት ብቻ ሳይሆን ማንኛውንም በምታደርገው ነገር ሁሉ ስኬታማ መሆን ትችላለህ። ለዚህም ብለን አባትህና እኔ ወደ ኢስላማዊ ትምህርት ቤት እንልክሃለን። ትምህርት ቤቱም በመልካም ባህሪ እንደሚያንፅህም ተስፋ እናደርጋለን።

ሐዲ: በጣም አመሰግናለሁ እማየ። ለዚህም ሆነ ለመጭው አለም የተሻለን ነገር እንደምትመኙልኝ አውቃለሁ። አሁን እንዴት ተዝኪያ ማድረግ እንደምችል ንገሩኝ።

አባት: ይህ እስከ ሂወትህ ፍፃሜ ድረስ የሚዘልቅ ነው ሐዲ። ምክኒያቱም እንደነገርኩህ ሂወት በፈተና የተሞላች ናት። ቁርአንና የረሱልን(ሰ.ዐ.ወ) መንገድ እና ምሳሌዎቹን ልታጠና ይገባል። በሁሉም ስራዎችህ ጥሩና ጠንካራ ሙስሊም ልትሆን ይገባል። ሙሉ ሂወትንህን ከመልካም ስራዎች ጋር ኢማንህን ጠንካራ ለማድረግና ኢህሳን ደረጃ ላይ ለመድረስ ጥረት አድርግ።

ሐዲ: በዚህ ረጅም ጉዞ ሊያግዘኝ የሚችል የምተገብረው ነገር አለ?

እናት: አዎ! ማንኛውንም ስራ በምትሰራበት ጊዜ በሶላትህ በጥናትህ ወ.ዘ.ተ ሁሉ ለአሏህ ቅን ለመሆን የቻልከውን ሁሉ አድርግ።

ሐዲ: የተቻለኝን ሁሉ አደርጋለሁ። አሏህ በትምህርቴም በሂወቴም ስኬታማ ያደርገኝ ዘንድ እለምንሃለሁ።

እናት: አሏህ ይቀበልህ ሐዲ።

ሐዲ: እንዳልረሳ እፈራሁ? አባት: አሏህ ያስታውስሃል ፍላጐቱ ካለህ ወጣት እያለሁ አስተማሪየ ያስተማሩኝን ልትሰራ ትችላለህ።

ሐዲ: አባየ ምንድ ነው ያስተማሩህ?

አባት: የዝርዝር ስራዎች እቅድ የሚባል ዝርዝር ነገሮችን ሰጡኝ። በእያንዳንዱ ቀን መጨረሻ ከመተኛቴ በፊት ሁሉንም ጥያቄዎች ቀን ስለ ሰራኋቸው ስራዎች እንዳስታውስ ነገሩኝ። ሁሉንም ወይም አብዛሃኛውን ጥያቄ አዎ! ብየ ከመለስኩ ብዙ መልካም ስራዎችን ሰርቻለሁ መጥፎ ስራዎችን ደግሞ አስዎግጃለሁ ማለት ነው። ለዚህም ደስተኛና አሏህን አመስጋኝ እንድሆን ነገሩኝ። አብዛሃኛውን አላደረኩም ብየ ከመለስኩ በእለት ተእለት ኢስላማዊ ተግባሬ ወድቂያለሁ ማለት ነው። አሏህን ምህረት ልጠይቅና የተሻለን ነገር በቀጣዩ ለመስራት መሞከር እንዳለብኝ ነገሩኝ።

ሐዲ: ተመሳሳይ ዝርዝር ነገሮችን ታዘጋጅልኛለህ አባየ?

አባት: አዎ! በትክክል አዘጋጅልሃለሁ።


<> Like Youth-Mission page and let your friends to interact with the page by inviting them to the page and Share with us your Islamic writings. Be part of the mission by having active involvement.

page:
http://facebook.com/youth.mission29

website:
http://youth-mission.mobie.in

{.♥.° ኑ ስለ ኢስላም እንተዋወስ °.♥.}
'~'-.,__,.-'~'
_,.-'~''~'-.,_
©የወጣቱ ተልእኮ

1595

የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
free book gift

Download Islamic Books
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ

Important Web Links


free book gift

free book gift

free book gift

ስለወጣቱ ተልዕኮ ምንነት ለማወቅ እዚህ ላይ ክሊክ ያድርጉ

Copyright©Youth-Mission የወጣቱ ተልዕኮ